የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች ወደ የቤታቸው?

የሀዲያ ሆሳእና ተጨዋቾች ከደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ አሁን ከነበሩበት ሆቴል መውጣታቸው ታውቋል።

የዞኑ እምክትል አስተዳዳሪ የመሩት ስብሰባ ያለስምምነት በመጠናቀቁ ተጨዋቾቹ ክፍያችን ሲፈጸም እንመለሳለን በማለት ወደየቤታቸው እየሄዱ መሆናቸው ታውቋል።
ይህም ማክሰኞ ምሽት 1 ሰአት ከአዳማ ከተማ ጋር ያለባቸውን ጨዋታ ላያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ ስልክ ቢጠራም ባለመነሳቱ የክለቡን ምላሽ ማወቅ አልተቻለም።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport