በብዙ ወዝግብ ታጅበዉ አመቱን ያጠናቀቁት ሀድያ ሆሳዕናዎች ምንም እንኳን በሊጉ ጥሩ ጅማሮን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም በጊዜ ሂደት ግን ዉጤታቸዉ እንደ አጀማመራቸው ሳይሆን ቀርቶ ሊጉን በአራተኝነት ደረጃ ማጠናቃቸዉ ይታወሳል። በተጨማሪም ተጫዋቾቻቸዉ ከክለቡ ጋር በገቡት አለመግባባት ሞክንያት የመጨረሻዎቹን የሊጉን ጨዋታዎች በታዳጊ ቡድኑ ተጫዋቾች ለመጫወት ሲገደዱም ተመልክተናል።
ሀድያዎች ለቀጣዩ የዉድድር አመት የበለጠ ተጠናክረዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸው ይታወቃል።
ዋና አሰልጣኝ ከሾሙ በኋላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ በመቀላቀል እና የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ሀድያዎች አሁን ደግሞ የአንበሉን ሔኖክ አርፌጮን ዉል ለተጨማሪ ሁለት አመት ማራዘማቸዉ ታዉቋል።

- ማሰታውቂያ -
የዉድድር አመቱን በጥሩ ብቃት ማጠናቀቅ የቻለዉ አማካዩ ሔኖክ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በመጨረሻም በሀድያ ቤት ለመቆየት ከስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።
ተጫዋቹ ዉሉን ከፈረመ በኋላ ለሀትሪክ ስፖርት በሰጠዉ አስተያየትም ” ከክለቡ አመራሮች ጋር በደንብ እንደተነጋገሩና በዉድድር አመቱ የተፈጠሩት ዉዝግቦች በቅርቡ እልባት እንደሚያገኙ በመተማመን ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ተጫዋቹን በክለቡ እንዲቆይ ያደረገዉ ሌላኛው ነገር ደግሞ ደጋፊዎች ለሱ ያላቸዉ የተለየ ፍቅር እንደሆነ የሚናገረዉ ተጫዋቹ ለክለቡ ያለው ፍቅር የላቅ እንደሆነ ሲገልፅ! ምንም እንኳን ከተለያዩ ክለቦች የእናስፈርምህ ጥያቄ ቢቀርብለትም በመጨረሻም ምርጫዉ በሀድያ ሆሳዕና ቤት መቆየት መርጫው መሆኑን ገልጸዋል ‘።
በተያያዘም ክለቡ ሀድያ ሆሳዕና በቅርቡ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቅል እና የነባሮቹን ዉል እንደሚያድስ ሀትሪክ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል።


