በመጀመሪያው ሳምንት በመቻል አንድ ለዜሮ ተሸንፈዉ ወደ ዛሬዉ ጨዋታ የመጡት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከመመራት ተነስተው ሲዳማ ቡናን አራት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችለዋል።
በጨዋታ ረገድ ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴን የተመለከትንበት የመጀመሪያው አጋማሽ ገና በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ተስተናግዶበታል። በዚህም ሄኖክ አርፌጮ ደግፌ አለሙ ላይ የሰራዉን ጥፋት ተከትሎ የተገኘዉን የቅጣት ምት አማካዩ ፍሬዉ ሰለሞን ሲያሻማዉ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ያኩቡ መሐመድ በጭንቅላቱ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታዉ ለመመለስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሀድያዎች ምንም እንኳን ዉጥናቸዉ ሰምሮ ግብ ማስቆጠር ባይችሉም በባየ ገዛኸኝ እና በፍሬዘር ካሳ ተከታታይ ድንቅ የሚባሉ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። በተቃራኒው በተከላካዩ ያኩቡ ግብ ጨዋታዉን በመመራት ላይ ይገኙ የነበሩት ሲዳማዎች በአጋማሹ ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ከዕረፍት መልስ እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ የአቻነት ግብ ለማግኘት በጥሩ አጨዋወት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሀድያዎች ዉጥናቸዉ ሰምሮ በ60ኛዉ ደቂቃ አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም የሲዳማ ቡና ተከላካዮች የሰሩትን የቅብብል ስህተት ተጠቅሞ ወጣቱ ተጫዋች ብሩክ ማርቆስ ከርቀት አክርሮ በመምታት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ወደ ጨዋታዉ ከመመለስ ይልቅ በተደጋጋሚ ስህተት ይሰሩ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በ66ኛዉ ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ግብ ለማስተናገድ ተገደዋል። በዚህም በድጋሚ የሲዳማ ቡና ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተከትሎ ባየ ገዛኸኝ ያቀበለዉን ኳስ አማካዩ ፍሬዉ ሰለሞን ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከመመራት ወደ መምራት የተሸጋገሩት ነብሮቹ በጨዋታው ይበልጥ የማጥቃት ሀይላቸዉን አጠናክረዉ የቀጠሉ ሲሆን በ89ኛዉ ደቂቃ ላይም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በዕለቱ ድንቅ የነበረዉ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን ከቀኝ መስመር ያቀበለዉን ኳስ ፀጋየ ወደ ግብነት ቀይሮ የቡድኑን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችሏል።
መደበኛው ዘጠና ደቀቃ ተጠናቆ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ደግሞ ነብሮቹ አራተኛ የማሸነፊያ ግባቸዉን ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም መሀል ሜዳ አካባቢ የቸገኘዉን ኳስ ሔኖክ አርፌጮ ሲያሻማ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ፀጋየ ለባየ ገዛኸኝ አመቻችቶ አቀብሎት አጥቂዉ ወደ ግብነት ቀይሮ የነብሮቹን የግብ መጠን ወደ አራት ከፍ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዚህም ሀድያ ሆሳዕና 4ለ1 በሆነ ዉጤት ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ችሏል።ነብሮቹ ከመመራት ተነስተዉ ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ችለዋል !
በመጀመሪያው ሳምንት በመቻል አንድ ለዜሮ ተሸንፈዉ ወደ ዛሬዉ ጨዋታ የመጡት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከመመራት ተነስተው ሲዳማ ቡናን አራት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችለዋል።
በጨዋታ ረገድ ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴን የተመለከትንበት የመጀመሪያው አጋማሽ ገና በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ተስተናግዶበታል። በዚህም ሄኖክ አርፌጮ ደግፌ አለሙ ላይ የሰራዉን ጥፋት ተከትሎ የተገኘዉን የቅጣት ምት አማካዩ ፍሬዉ ሰለሞን ሲያሻማዉ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ያኩቡ መሐመድ በጭንቅላቱ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታዉ ለመመለስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሀድያዎች ምንም እንኳን ዉጥናቸዉ ሰምሮ ግብ ማስቆጠር ባይችሉም በባየ ገዛኸኝ እና በፍሬዘር ካሳ ተከታታይ ድንቅ የሚባሉ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። በተቃራኒው በተከላካዩ ያኩቡ ግብ ጨዋታዉን በመመራት ላይ ይገኙ የነበሩት ሲዳማዎች በአጋማሹ ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከዕረፍት መልስ እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ የአቻነት ግብ ለማግኘት በጥሩ አጨዋወት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሀድያዎች ዉጥናቸዉ ሰምሮ በ60ኛዉ ደቂቃ አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም የሲዳማ ቡና ተከላካዮች የሰሩትን የቅብብል ስህተት ተጠቅሞ ወጣቱ ተጫዋች ብሩክ ማርቆስ ከርቀት አክርሮ በመምታት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ወደ ጨዋታዉ ከመመለስ ይልቅ በተደጋጋሚ ስህተት ይሰሩ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በ66ኛዉ ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ግብ ለማስተናገድ ተገደዋል። በዚህም በድጋሚ የሲዳማ ቡና ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተከትሎ ባየ ገዛኸኝ ያቀበለዉን ኳስ አማካዩ ፍሬዉ ሰለሞን ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከመመራት ወደ መምራት የተሸጋገሩት ነብሮቹ በጨዋታው ይበልጥ የማጥቃት ሀይላቸዉን አጠናክረዉ የቀጠሉ ሲሆን በ89ኛዉ ደቂቃ ላይም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በዕለቱ ድንቅ የነበረዉ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን ከቀኝ መስመር ያቀበለዉን ኳስ ፀጋየ ወደ ግብነት ቀይሮ የቡድኑን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችሏል።
መደበኛው ዘጠና ደቀቃ ተጠናቆ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ደግሞ ነብሮቹ አራተኛ የማሸነፊያ ግባቸዉን ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም መሀል ሜዳ አካባቢ የቸገኘዉን ኳስ ሔኖክ አርፌጮ ሲያሻማ በጥሩ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረዉ ፀጋየ ለባየ ገዛኸኝ አመቻችቶ አቀብሎት አጥቂዉ ወደ ግብነት ቀይሮ የነብሮቹን የግብ መጠን ወደ አራት ከፍ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዚህም ሀድያ ሆሳዕና 4ለ1 በሆነ ዉጤት ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ችሏል።