By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል ሲደመድም ፤ መዉረዳቸዉን ያረጋገጡት ሻሸመኔዎችም ሀምበሪቾን በማሸነፍ የሊጉን ቆይታቸዉን አገባደዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ወልቂጤ ከተማየጨዋታ ዘገባሻሸመኔ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችአዳማ ከተማሀምበሪቾ ድራሜ

ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል ሲደመድም ፤ መዉረዳቸዉን ያረጋገጡት ሻሸመኔዎችም ሀምበሪቾን በማሸነፍ የሊጉን ቆይታቸዉን አገባደዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ባሳለፍነዉ ሳምንት በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠዉ ወልቂጤ ከተማ አዳማ ከተማን 1ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።

በዋና ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ መሪነት ቀን ዘጠኝ ሰዓት በጀመረዉ ጨዋታ ገና በጊዜ ወጣቱ የፊት መስመር ተጫዋች ቢኒያም አይተን በአዳማ ከተማ በኩል ከቦና አሊ የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ የግቡ ቋሚ በመለሰበት ሙከራ የጨዋታ እንቅስቃሴያቸዉን የጀመሩ ሲሆን ፤ በዚህ ሂደትም በተደጋጋሚ ዘደ ወልቂጤ ከተማ የግብ ክልል በመድረስ እና የመስመር ተጫዋቾቻቸዉን በመጠቀም ዕድሎችን በመፍጠር ግቦችን ለማስቆጠር ሲጥሩ ፤ በተቃራኒው ሰራተኞቹ ደግሞ በእንቅስቃሴ ረገድ በሚቆራረጡ ኳሶች እና የመሐል ላይ ቅብብሎች ለመጫዋት ሲሞክሩ ተስተዉሏል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታዉ በ21ኛዉ ደቂቃ ላይ ተከላካዩ መሳይ ጳውሎስ ቢኒያም አይተን ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት ቦና አሊ መትቶት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ግብ ጠባቂዉ ፋሪስ አለሙ ኳሷን አምክኗታል። ጫና ፈጥረዉ መጫወታቸዉን የቀጠሉት አዳማዎች በ31ኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ በጀሚል ያቆብ አማካኝነት ግሩም ሙከራ አድርገዉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የግቡ ቋሚ ኳሷን መልሷታል።

- ማሰታውቂያ -

ደካማ የነበሩት ክትፎዎቹ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዉ ጋዲሳ መብራቴም ፔናሊቲውን መምታት ችሎ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ ወደ ዉጭ ወጥታለች። ከዕረፍት መልስ አዳማ ከተማዎች የማጥቃት ሀይላቸዉን አሻሽለዉ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን ፤ በተቃራኒው ብልጫ የተወሰደባቸዉ ወልቂጤ ከተማዎች ደግሞ ያን ያህል ተጠቃሽ ሙከራዎችን ማድረግ ሳይችሉ ቀጥለዉ ይባስኑ በ61ኛዉ ደቂቃ ላይ አልሀሺምን በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ አጥተዉታል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ በ10 ተጫዋቾች እየተጫወቱ የነበሩት ወልቂጤዎች በ72ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ተመስገን በጅሮንድ ያሻገረዉን ኳስ ተከላካዮች ሲመልሱት ያገኘዉ አዳነ በላይነህ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡ ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል መደምደም የቻለበትን ዉጤት እንዲያስመዘግብ አድርጓል።

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ሁለቱ መውረዳቸዉን ያረጋገጡት ሻሸመኔ እና ሀምበሪቾ ባደረጉት ጨዋታ ሻሸመኔ ከተማ 3ለ1 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በተመጣጣኝ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ እና በሙከራ ረገድ ተቆጥቦ በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች የምሽቱ ጨዋታ ገና በጊዜ ተመስገን አሰፋ ከቅጣት ምት በሞከራት ኳስ ሀምበሪቾን ቀዳሚ ለማድረግ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም በሻሸመኔዉ ግብ ጠባቂ ኬኒ ሰይድ ድንቅ ብቃት ኳሷ መክናበታለች።

በዚህ ሂደት የጀመረዉ ጨዋታም ለ18 ያክል ደቂቃዎች ቀጥሎ ግብ ተቆጥሮበታል ፤ በዚህም ሳጥን ውስጥ የሻሸመኔዉ አጥቂ ስንታየሁ መንግስቱ ያቀበለዉን ኳስ ሱራፌል ሙሉዎርቅ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን ሻሸመኔ ከተማ መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት ሻሸመኔዎች ዳግም በ37ተኛዉ ደቂቃ ግብ አክለዋል። በዚህም አብዱልቃድር ናስር ከመሐል የተቀበለዉን ኳስ ለአጥቂዉ ስንታየሁ አቀብሎት አጥቂዉም ሁለተኛዋን ጎል በጎሩም ብቃት አስቆጥሯል።

ከሰባት ደቂቃዎች በኀላ ዳግም አጥቂዉ ስንታየሁ ተጫዋቾችን ጭምር በማለፍ ለራሱ ሁለተኛ ለክለቡ ደግሞ ሶስተኛ ግብ አስቆጥሮ አጋማሹ በሻሸመኔ ከተማ ሶስት ለዜሮ መሪነት ተገባዷል። ከዕረፍት መልስ ሁለቱም ክለቦች ተመጣጣኝ የመሐል ሜዳ እንቅስቃሴን እያስመለከቱን የቀጠሉ ቢሆንም ነገር ግን ዕድሎችን በመፍጠር እና ግብ በማስቆጠሩ ረገድ ውስንነቶች ተስተዉሎባቸዋል።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም መደበኛዉ ዘጠና ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪዉ ደቂቃ 90+5 ላይ የሻሸመኔዉ ተከላካይ ኢብሳ ኳስ በዕጅ መንካቱን ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት ኤፍሬም አሻሞ አስቆጥሮ ጨዋታዉ በሻሸመኔ ከተማ 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታድየም ይደረጋል
Next Article በመጨረሻም አዲስ አዳጊዉ ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ እየተመራ የሊጉን የዋንጫ ክብር ማሳካት ችሏል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዜናዎችሰበታ ከተማሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ሲዳማ ቡና እና ሰበታ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 4 years ago
​ፋሲል ከተማ በአዲስ አበባ ድል ቀንቶታል
የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ድል ተቀዳጅቷል
አልጄሪያዎች እናንተ ሩጫ እንጂ ኳስ አትችሉም ብለውን አሸንፈናቸው የተናደዱበትን ጊዜ መቼም አልረሳሁም” ብዙነህ ወርቁ /በሶ
የፕሪሚየር ሊጉ ደጋፊዎች የሚፋለሙበት ውድድር ሊካሄድ ነው
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?