በሀያ አንደኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር የመጨረሻ ዕለት ጨዋታ ቀን 10:00 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ሀድያ ሆሳዕናን አሸንፏል ።
የነብሮቹን የጨዋታ የበላይነት እያስመለከተ በጀመረዉ መርሐግብር ገና በመባቻዉ በ9ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሀድያዎች መሪ መሆን ችለዋል ። በዚህም ባለ ግራ ዕግሩ ሳሙኤል ዮሐንስ ከርቀት ገና በጊዜ ድንቅ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታውን መምራት ጀምረዋል። ገና በጊዜ ግብ የተቆጠረባቸዉ እና በእንቅስቃሴም አጀማመሩ ላይ ብልጫ የተወሰደባቸዉ ሲዳማ ቡናዎች በሂደት ወደ ጨዋታዉ ገብተዉ በቡልቻ ሹራ አማካኝነት ከግራ መስመር በኩል ድንቅ የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ችለዋል።
በተደጋጋሚ ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት ሲዳማዎች አጋማሹ ሳይገባደድ የአቻነት ግብ አግኝተዋል ። በዚህም ቡልቻ ሹራ ወደ መስመር ተጠግቶ የተገኘዉን የቅጣት ምት ኳስ ሲያሻማ ራሱ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ አድርጓል። የአቻነት ግብ ከተቆጠረ በኋላ ተመጣጣኝ የጨዋታ ፉክክር እያስመለከተን በቀጠለዉ ጨዋታ ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር አጋማሹ ተገባዷል።
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽም ሁለቱም ክለቦች እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁሉ የጨዋታዉ የመሐል ሜዳ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ከመጣር በዘለለ በሙከራ ረገድ ደካማ ሆነዉ የቀጠሉ ሲሆን ፤ በ70ኛዉ ደቂቃ ላይ ግን በሂደት ብልጫ መዉሰድ የቻሉት ሲዳማዎች ጨዋታውን መምራት ጀምረዋል ። በዚህም ቡልቻ ሹራ ከማይክል ኪፕሩል ተቀብሎ ለራሱ ለተጫዋቹ ያመቻቸለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር ሲዳማን ከመመራት ወደ መሪነት አሸጋግሯል።
በእጃቸዉ የነበረዉን ወርቃማ እድል አሳልፈዉ የሰጡት ሀድያ ሆሳዕናዎች በርከት ያሉ የማጥቃት ባህሪ ያላቸዉን ተጫዋቾች ቀይረዉ ወደ ሜዳ ቢያስገቡም ዉጥናቸዉ ሰምሮ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታዉ በሲዳማ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዕሁለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በአዳማ ከተማ የ2ለ1 ሽንፍት አስተናግዷል ።
ምሽት 1:00 ሰዓት ሲል በዋና ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘዉ መሪነት በጀመረው ተጠባቂ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ሁለቱም ክለበች ተመጣጣኝ በሚባል የሜዳ ላይ ፉክክር ማራኪ የጨዋታ እንቅስቃሴ ሲያስመለክቱን የነበረ ሲሆን ፤ ሙከራ ለማድረግ ግን 24 ደቂቃዎችን መጠበቅ ግድ ብሎ ነበር ። በዚህም ቡናማዎቹ ከቀኝ መስመር በኩል በአብዱልከሪም ወርቁ አማካኝነት ያሻገሩትን ኳስ አጥቂዉ አንተነህ ተፈራ በጭንቅላቱ ወደ ግብ ቢልክም ኳሷን ግብ ጠባቂዉ ሰይድ ተቆጣጥሯል።
ከዚች ሙከራ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላም አዳማ ከተማዎች ጥሩ ዕድል መፍጠር ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ከግራ መስመር በኩል ቢኒያም አይተን ያቀበለዉን ኳስ ዮሴፍ ታረቀኝ ወደ ግብነት ቀየረዉ ተብሎ ቢታሰብም የግብ ዘቡ በረከት ኳሷን እንደምይም አክሽፏታል። በ29ነኛዉ ደቂቃ ላይ ግን በጥሩ ቅብብል ቡናማዎቹ ሳጥን ውስጥ ከደረሱ በኋላ ሱራፌል ዐወል አማኑኤል አድማሱ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት መስፍን ታፈሰ ቢመታዉም ኳሷን አምክኗታል።
በ31ኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ በመልሶ ማጥቃት የቡናማዎቹ ሳጥን ውስጥ የደረሱት አዳማዎች ጀሚል ያዕቆብ ወደ ግብ ሞክሯት የተመለሰችዉን ኳስ ዮሴፍ ከመረቡ ጋር ቀላቅሎ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል። ከዕረፍት መልስ የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረዉ መጫወት የቀጠሉት ቡናማዎቹ በ50ኛዉ ደቂቃ ላይ አብዱልከሪም ወርቁ ያቀበለዉን ኳስ አማኑኤል አድማሱ በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም ግብ ጠባቂዉ ሰይድ ሀብታሙ ኳሷን ተቆጣጥሯል።
የመሪነት ግብ ካስቆጠሩ በኋላ በይበልጥ ወደ ራሳቸዉ የግብ ክልል አዘንብለዉ በመጫወት ጥንቃቄን መርጠዉ አልፎ አልፎም በመልሶ ማጥቃት አደጋን ለመፍጠር ሲጥሩ የነበሩት አዳማ ከተማዎች በ63ተኛዉ ደቂቃ ከቅጣት ምት በሱራፌል ምክንያት ድንቅ ሙከራን ቢያደርጉም ኳሷ የገቡን አግዳሚ ነክታ ወደ ዉጭ ወጥታለች።
በተደጋጋሚ ጨና ፈጥረዉ በመጫወት ዕድሎችን ለማግኘት ይጥሩ የነበሩት ቡናማዎቹ መነሻቸዉን ከአብዱልከሪም ባደረጉ ኳሶችን አጥቂዎቹ መስፍን ታፈሰ እና አንተነህ ተፈራ ጥሩ ጥሩ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ዉጥናቸዉ ሰምሮ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዉ በጨዋታው በአዳማ ከተማ 1ለ0 ተሸንፈዋል።