ጋሞ ጨንቻ የቀድሞው ተጫዋቹን ስራ አስኪያጅ ሲያደርግ አሰልጣኙ በኮንትራቱ መሠረት ይቀጥላል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደገው ጋሞ ጨንቻ ወደ አስራ ዘጠኝ የሚደርሱ የቦርድ አባላትን ማዋቀሩ የሚታወስ ሲሆን ቦርዱም ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በጉዳት ከእግር ኳስ የራቁትን የቀድሞው የእህል ንግድ እና ደብረብርሃን ብርድ ልብስ ተጫዋች የነበሩት እና በአሁኑ ሰዓት የጋሞ ዞን ብልፅግና የፓለቲካ እና ህዝብ ግንኙነት ሀላፊውን አቶ አብዱልሀሚድ መሐመድን ዋና ስራ አስኪያጅ በማድረግ ሲሾም በክለቡ የሁለት አመት ውል ያላቸው ክለቡን ከከፍተኛ ሊጉ ያሳደጉት አሰልጣኝ ማቲዮስ ለማም በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ወስኗል።

አስተያየት ይስጡ