ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂን አስፈረመ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በአጭር ጊዜ ድንቅ መሆን ከቻሉ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ይጠቀሳል። ከመቱ ከተማ ከተነሳ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ ወሎ ኮምቦልቻ በፕሪምየር ሊጎቹ ጅማ አባጃፋር ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ባህርዳር ከተማ እና ላለፉት አራት አመታት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ሲጫወት የቆየው ከክለቡም ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ከማንሳት በዘለለ ለሁለት ጊዜ ያህል የዓመቱ የሊጉ ምርጡ ግብ ጠባቂ በመባል የተመረጠው የግብ ዘቡ ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል የተቃረበ ቢመስልም ማረፊያው የቀድሞው አሰልጣኙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ