የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ሽመክት ጉግሳ(ኢትዮ ኤሌትሪክ ) የመታወቂያ ቁጥር እሁድ መስከረም 12 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 84 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. አበበ ጥላሁን(አርባምንጭ ከተማ) የመታወቂያ ቁጥር አርብ መስከረም 10 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 83 ኛ ደቂቃ ላይ የጠብ አጫሪነት ወይም የሃይለኝነት ድርጊት በመፈጸም በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 64 በተቁ 2 (U) መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. አስጨናቂ ፀጋዬ(ሀዲያ ሆሳዕና) የመታወቂያ ቁጥር አርብ መስከረም 10 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 54 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35 በተቁ 1 (መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ- ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
4.አዳማ ከተማ ክለቡ ከከስሁል ሽረጋር በነበረው የIኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ቅድመ ስብሰባ ወቅት ስለመቅረቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ክለቡ ለፈፀመው ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቁ 7 መሰረት ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።