የሀገሪቱን የግዛት አንድነትና የህዝቦቿን ነጻነት ለማረጋገጥ በጦርነት አውድማው እየተፋለመ ላለው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ቀጥሏል።
በእግር ኳሱ አደባባይ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጨዋቾችና አሰልጣኞች የአንድ ወር ደመወዝ ለመስጠት መወሰናቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች የሙያ ማህበር ከአባላቱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ 100ሺህ ብር ለመስጠት መወሰኑን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው አስታውቋል።
ፕሬዝዳንቱ ማህበሩ በድጋፉ ደስተኛ መሆኑን ገልጾ ድጋፉ በተለያየ አማራጭም እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ