መነሻ ገጽ ዜናዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ ?
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ ?

አጋራ
አጋራ

ለቀጣዮቹ አራት አመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽንን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የሚደረገው ምርጫ ጉዳይን በተመለከተ መረጃን ይዣለሁ።

በየአራት አመቱ የኢትዮጵያን እግር ኳስ በበላይነት ለመምራት በዋናነት የፕሬዝዳንታዊ እንዲሁም ደግሞ የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ይደረጋል። ባለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን አቶ ኢሳያስ ጂራ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ለሦስተኛ ጊዜ ለመወዳደርም የምርጫ ደንቡን ለማሻሻል ጥያቄ ማቅረባቸውም ይታወሳል። ከወራት በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በፌድሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት አንድ ፕሬዝዳንት ለሁለት የምርጫ ዘመን ብቻ ነው በፕሬዝዳንትነት መምራት የሚችለው የሚለውን ህግ በመሰረዝ ማሻሻያ በማድረግ ለሦስተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት ለመሆን መወዳደርን የፈለጉት እና የማሻሻያ ጥያቄን በወቅቱ ያቀረቡት አቶ ኢሳያስ ጂራ እስከ አሁን መተዳደሪያ ደንቡ ይሻላል የሚለው ጉዳይ እልባት ባያገኝም ከቀጣዩ አንድ ወር በኋላ ግን የስልጣን ዘመናቸው ይጠናቀቃል።

ይህንንም ተከትሎ ለቀጣዮቹ አራት አመታት ፌድሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት የሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ እና ምርጫን በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን እስከ አሁን ያለው ነገር ባይኖርም የፊታችን ነሀሴ 20/2018 ምርጫን ለማድረግ ዕቅድ እንዳለ ያገኘሁት መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ዝምታን ቢመርጥም ስለ ምርጫው እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ክልሎች ስለሚወክሏቸው ተወዳዳሪ እጩዎች መረጃዎችን እየሰበሰብኩ የማቀርብላችሁም ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...