ሉሲዎቹ የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል

ለኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በጨዋታ ጊዜ በሚከሰት ግጭት ጡት ላይ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የሚረዳ የጡት ግጭት መከላከያ ( የስፖርት ብራ ) በቦስተን ነዋሪ ከሆኑት ከአቶ ዳዊት ጌታቸው በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዳራሽ የፌደሬሽኑ ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ፤ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እና አምበሏ ሎዛ አበራ በተገኙበት ተበርክቶላቸዋል ።

ድጋፉን ያደረጉት አቶ ዳዊት ጌታቸው በወቅቱ እንደገለፁት የትጥቅ ድጋፉ የተለያየ መጠን ያለው ሆኖ ለ30 የቡድኑ አባላት የሚያገለግል ነው ብለዋል ፤ በተጨማሪም ለቡድኑ ድጋፍ ማድረግ የጀመሩት ከ8 አመት በፊት ጀምሮ መሆኑን ያሁኑ ድጋፍም ለ4ኛ ጊዜ ያደረጉት እንደሆነ ከዚህ በኋላም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *