የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

- ቦና ቦካ (ነገሌ አርሲ) : ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ36ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 15 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። - ፀጋአብ ዮሐንስ (ምድረ ገነት ሽረ) : ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ36ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 75 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። - ሚካኤል በየነ (ምድረ ገነት ሽረ) /ወጌሻ/ : ክለባቸው ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ36ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 77 ኛ ደቂቃ ላይዳኛን ለመማታት በመሞከር እና አጸያፊ ስድብ በመሳደብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ፡፡
ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ደንብ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 6 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ - አብዱሰላም ዩሱፍ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 9 ጨዋታዎች የቢጫ
ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ፡፡
- ወላይታ ድቻ-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ‐ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- መቻል-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-አዳማ ከተማ
- ምድረ ገነት ሽረ -ድሬደዋ ከተማ
- አዳማ ከተማ-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-ባህርዳር ከተማ
- ኢትዮጵያ መድን-ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-ሸገር ከተማ
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ቢንያም በቀለ (ኢትዮ ኤሌትሪክ ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ -አዳማ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ሽገር ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ-ኢትዮጵያ ቡና
- ወላይታ ድቻ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ዘላለም አበበ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።
- ኢትዮጵያ ቡና-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቻል
- አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡና
- ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ሄኖክ አርፊጮ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ከታች በተጠቀሱት 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ባህርዳር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- መቐለ 70 እንደርታ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሃዋሳ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ሀዲያ ሆሳዕና-ሃዋሳ ከተማ
- ሲዳማ ቡና-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ዳግም ንጉሴ(ሀዲያ ሆሳዕና) የመታወቂያ ቁጥር EFF-18-599 ከታች በተጠቀሱት 15 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።
- ሀዲያ ሆሳዕና-ኢትዮጵያ መድን
- ሸገር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ቅዱስ ጊዮርጊስ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሃዋሳ ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ምድረ ገነት ሽረ
- ድሬደዋ ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ፋሲል ከነማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ባህርዳር ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና-አዳማ ከተማ
- ሀዲያ ሆሳዕና-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ሃዋሳ ከተማ
- ሲዳማ ቡና-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና-ፋሲል ከነማ
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ኢትዮጵያ መድን -አዳማ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮጵያ መድን
- ኢትዮጵያ መድን -ባህርዳር ከተማ
- ኢትዮጵያ መድን -ሃዋሳ ከተማ
- መቻል-ኢትዮጵያ መድን
- ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ሀዲያ ሆሳዕና : ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ36 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ዳግም ንጉሴ
- ሄኖክ አርፈጮ
- ብሩክ በየነ
- ኦውሱ እንድሪውስ
- ተመስገን ብርሃኑ
- በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ብርሀኑ በቀለ (ተጫዋች-ሲዳማ ቡና) : ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ36 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ውድድሩ ካለቀ በኋላ ሃይማኖታዊ መልእክት ስለማስተላለፉ ሪፖርት ተደርጎበታል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.2(ተራ ቁጥር 6) መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡
- አዲሴ ካሳ (አርባ ምንጭ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ) ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው የ36ኛ ሳምንት ግጥሚያ ከጨዋታ በኋላ በቀጥታ የቴሊቭዥን ስርጭት ባደረጉት ቃለመጠይቅ የፌዴሬሽኑን ስምና ዝና ያጎደፈ የፌዴሬሽኑን እና የአክሲዮን ማህበሩን አሰራር (ከወራጅ ቡድን ጋር በተያያዘ) በሃሰት ላይ የተመሰረተ መረጃ ስለመስጠታቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል። ስለሆነም አሰልጣኙ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 2(ሀ) መሠረት 6/ ስድስት ወር/ እንዲታገዱና ብር 10,000 /10 ሺህ / እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- የስታድየም ለውጥ
በአዲስ አበባ ስታድየም ሊደረጉ የነበሩት የ37ኛ እና የ38ኛ ጨዋታዎች መርሀ ግብር ወደ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታድየም የተዘዋወሩ መሆኑን የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ያሳውቃል።
አስተያየት ይስጡ