አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን በማስፈረም ወደ ዝውውር የገባው ድሬዳዋ ከተማ አዳዲስ እና የነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘም ጀምሯል።
መሀመድ ኑር ናስር፣ አህመድ ረሺድ፣ አብዱሰላም ዩሱፍ አዲስ ቡድኑን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሲሆኑ አምና ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ግብ ጠባቂ አብዩ ካሳዬም ውሉን አራዝሟል።
ባለፉት ሁለት አመታት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች መሐመድ ኑር ናስር በጉዳት ምክንያት የተጠበቀውን ያህል በቡና ቤት ጎልቶ ባይወጣም በተሰለፈባቸው 15 ጨወታዎች ላይ 6 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ሌላ ክለቡን የተቀላቀለው ሁለገቡ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው እና የቀድሞ የድሬ ከተማ ተጫዋች አህመድ ረሺድ (ሽሪላ) ሲሆን አህመድ ረሺድ አምና እና ካቸምና ከአዳማ ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፏል፣ ሌላው ፈረሚ የግራ መስመር ተከላካዩ አብዱሰላም ዩሱፍ ነው አብዱሠላም ከሀምበሪቾ ጋር ምንም የተሳካ የውድድር አመት ባያሳልፍም በግሉ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ በይታገሱ አይን ውስጥ መግባት ችሏል።
ውላቸውን ካራዘሙት የአምና ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነው ወጣቱ ግብ ጠባቂ አብዩ ካሳዬ ሲሆን አብዩ በዘንድሮ የውድድር ዓመት አሳማኝ ብቃቱን በማሳየት የመጀመሪያ የቡድኑ ግብ ጠባቂ መሆኑ ይታወሳል።
- ማሰታውቂያ -
ሁሉም ተጫዋቾች ሁለት አመት ለመቆየት የፈረሙ ሲሆን ነገ የ2017 ዓ.ም የቅድመ ውድድር ዝግጅት በአዳማ ከተማ የሚጀምሩ ይሆናል።