አጫጭር የሀገር ውስጥ የዝውውር መረጃዎች
👉 ወጣቱ ግብ ጠባቂ አብዩ ካሳዬ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቷል። ከድሬዳዋ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ያለፉትን ስድስት አመታት በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው ወጣቱ የግብ ዘብ በድሬዳዋ ከተማ ከዚህ በፊት ያሰለጠኑትን አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ጥሪ ተቀብሎ ማረፊያው ፋሲል ከነማ ሆኗል።

ፋሲል ከነማ ከአዲሱ ፈራሚው በተጨማሪ ያለፉትን ሰባት አመታት ከወጣት ቡድን በማደግ ለክለቡ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረውን የተከላካይ አማካዩን አቤል እያዩን ውል ለተጨማሪ አመት ውሉን አራዝሟል።

👉 አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ በኢትዮጵያ መድን ይቀጥላሉ። ኢትዮጵያ መድንን ከሳምንት በፊት ቢረከቡም ትላንት በነበረው ዘገባዬ ከክለቡ ጋር በተፈጠሩ ምክንያቾች እንደማይቀጥሉ የገለፅንላችሁ ጉዳይ በመፈታቱ አሰልጣኙ በክለቡ የሚቀጥሉ ሲሆን ከነገ ዕርብ ጀምሮም ወደ ዝውውሩ ይገባሉ።

👉 ባህርዳር ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ አስፈርሟል። ክለቡን መቀላቀል የቻለው የመጀመሪያው ተጫዋች ወጣቱ የግብ ዘብ ሀይደር ሙደሲር ነው። የቀድሞው የወሊሶ ከተማ የግብ ዘብ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቆይታን ካደረገ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ባህርዳር ከተማ ሆኗል።
ሌላኛው የባህርዳር ከተማ አዲሱ ፈራሚ የመስመር አጥቂው ናትናኤል ጋቻፎ ነው። ከወላይታ ድቻ ከ20 አመት በታች ቡድን መነሻውን ካደረገ በኋላ ያለፉትን ሁለት አመታት በከፍተኛ ሊጉ ቦዲቲ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም አስደናቂው ወጣት ተጫዋች ባህርዳርን በይፋ ተቀላቅሏል።

👉 ኢትዮ ኤሌክትሪክ አካሉ አትሞን የግሉ አድርጓል። በቀኝ እና በመሐል ተከላካይነት ያለፉትን አራት አመታት በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈው ተጫዋቹ ማረፊያው ኤሌክትሪክ ሆኗል።

👉 ካፍ ዛሬ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉ ክለቦችን የዕርስ በዕርስ ድልድል ይፋ ሲያደግ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡና ከቡሩንዲው ኤግሌ ኖይር እና ከሱዳኑ አልሂላል ከሁለት አንዱ አሸናፊ መሆን የቻለውን ቡድን ሲገጥም የኢትዮጵያ ዋንጫ ባለቤቱ ወልዋሎ ደግሞ ከሱዳኑ አልሂላል አልሳሂሊ ጋር በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ተደልድሏል።


አስተያየት ይስጡ