ዛሬ ረፋድ ላይ በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው መርሀ ግብር ጨዋታቸውን ያደረጉት የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን የ አዳማ ከተማ ወጣት ቡድንን 7 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል ።
አዳማ ከተማዎች ቀድመው በ ዮሴፍ ታረቀኝ ግብ ቢመሩም የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን አከታትለው ባስቆጠሩት ጎሎች ማሸነፍ ችለዋል ።

ለ ኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን አቡበከር ናስር ፣ ዊሊያም ሰለሞን ፣ አብድልሀፊዝ ቶፊቅ ፣ ስንታየሁ መንግስቱ ፣ ሙህዲን ሙሳ ፣ ሀይሌ ገብረ ትንሳኤ እና ቸርነት ጉግሳ የ ማሸነፊያውን ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።
የ ኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን ነገ ረፋድ ወደ ባህር ዳር ከተማ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል ።
አስተያየት ይስጡ