ኢትዮጵያ ቡና ኮንጓዊ አማካይ አስፈረመ

በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ መሪነት በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት እና ሸገር ከተማን በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት በሜዳቸው የሚገጥሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዲሞክራቲክ ኮንጎዊውን የ25 አመት አማካይ ጁኒየር ማቩንጉን አስፈርመዋል።
ለሀገሩ ክለቦች ስትሪም እና ሴንት ሉፖፖ በመጫወት ያሳለፈው ይህ ተጫዋች ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ጥቂት የልምምድ ጊዜያት ካሳለፈ በኋላ ለክለቡ በይፋ ፊርማውን አኑሯል።
አስተያየት ይስጡ