በአራተኛ ሳምንት ሶስተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን አሸንፏል።
በሶስተኛዉ ሳምንት ወልቂጤ ከተማን 1ለ0 በሆነ ጠባብ ዉጤት ማሸነፍ ችለዉ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ያለ ዋና አሰልጣኛቸው ጨዋታዉ ለማድረግ ወደ ሜዳ ሲገቡ በተመሳሳይ ከቀያት በፊት አዲስ ዋና አሰልጣኝ የሾሙት ሲዳማዎች በምክትል አሰልጣኛቸው መሪነት ጨዋታቸዉን ጀምረዋል።
- ማሰታውቂያ -
ተመጣጣኝ የጨዋታ ፋክክር በተስተዋለበት የመጀመሪያ አጋማሽ ገና በ13ኛዉ ደቂቃ ላይ ድንቅ ሙከራ ተስተዉሎበታል። በዚህም በሲዳማዎች በኩል የቀኝ መስመር ተከላካዩ አማኑኤል እንዳለ ቀጥታ ወደ ግብ የላከዉ ኳስ ለጥቂት አንግሉን ገጭቶ ወደ ዉጭ ወጥቷል።
ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ በ17ኛዉ ደቂቃ ላይ ጫላ ተሽታ ከቀኝ መስመር ላይ ያሻገለረትን ኳስ መስፍን ታፈሰ ተቀልብሶ ወደ ግብ ቢሞክርም ለጥቂት ወጥታለች። ከዚች ሙከራ በኋላ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ በ19ኛዉ ደቂቃ ላይ አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ያቀበለዉን ኳስ መስፍን ታፈሰ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡናማዎቹን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታዉ ለመመለስ በቶሎ ጥረት ማድረግ የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች በፊት መስመር ተጫዋቹ አማኑኤል እና በአማካዩ ፍሬዉ ሰለሞን ጣቁሩ አማካኝነት በተከታታይ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም የግቡ አግዳሚ መልሶባቸዋል። በዚሂም ሁለቱ ክቦች ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ከዕረፍት መልስ ጠንከር ብለዉ የተመለሱት ሲዳማዎች በተደጋጋሚ በመስመር በኩል እና ወደ ፊት በሚጣሉ ኳሶች ተጋጣሚ በድንን ላይ ጫና ለመፍጠር ሲጥሩ በአንፃሩ ቡናማዎቹ በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ ምንም እንኳን የተሸሉ ቢሆን እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ በተደጋጋሚ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ለመድረስ ግን ሲቸገሩ ተስተውሏል።
የአቻነቷን ግብ ለማግኘት መቀስቀሳቸውን የቀጠሉት ሲዳማዎች በ75ኛዉ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በገባዉ ፀጋየ አበራ አማካኝነት ከርቀት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም በግብ ዘቡ በረከት አማረ ድንቅ ጥረት ኳሷ ግብ ከመሆን ከሽፋለች። ከዚች ሙከራ በኋላም በድጋሚ በ80ኛዉ ደቂቃ ላይ የግራ መስመር ተከላካዩ መሐሪ መና ያሻገረዉን ኳስ የመስመር አጥቂዉ ይገዙ ቦጋለ ሞክሮ ኳሷ ስትመለስ በአቅራቢያው የነበረዉ ያኩቡ መሐመድ ሞክሮ ለጥቂት ወጥታለች።
በዚህ ሂደት የቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም ኢትዮጵያ ቡናዎች ከዕረፍት መልስ ባስቆጠሩት ግብ 1ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸኘፍ ችለዋል።