ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ እና በብሔራዊ ቡድን ደረጃም ረዘም ላሉ አመታት በተከላካይነት በማገልገል ላይ የሚገኘዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አስቻለው ታመነ በመጨረሻም ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ወደ አዲስ ክለብ ማምራቱ ታውቋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም ለደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለዉ ተከላካዩ አስቻለው ታመነ በሁለት አመት የኮንትራት ውል የአሰልጣኝ ገ/ክርስቶስ ቢራራን ቡድን መቻልን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።