በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት በአሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ (ቲጋና) እና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመራ በውድድር አመቱ አርባ ሶስት ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ የአራተኝነት ስፍራን ይዞ ማጠናቀቅ የቻለዉ ፋሲል ከነማ በአዲሱ አሰልጣኙ ዉበቱ አባተ እየተመራ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚጀምርበት ዕለት ታውቋል።
በዚህም በዝውውር ገበያዉ ላይ በንፅፅር እንደ ሌሎቹ የሊጉ ክለቦች እምብዛም እንቅስቃሴ ያላደረገዉ እና ነገር ግን ጌታነህ ከበደን እንዲሁም ቃልኪዳን ዘላለምን የመሳሰሉ የጥራታቸዉ ደረጃ ከፍ ያሉ ተጫዋቾችን አስከአሁን ማስፈረም የቻለዉ ፋሲል ከነማ ከቀናት በኋላ ነሀሴ-11 በሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን እንደሚጀመር ክለቡ አስታውቋል።