የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት የተላለፉ ውሳኔዎች እና ያልተሰሙ ጉዳዮች !

 

የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር እና አመራር ከሰዓታት በፊት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ ሪፖርቶች መርምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል ።

በአምስተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ዘጠኝ ጎሎች ከመረብ ሲያርፉ አራት ጎሎች በፍፁም ቅጣት ምት ሲቆጠሩ የሀዋሳ ከተማው ምኞት ደበበ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆኖ በሳምንቱ አልፏል ።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በሳምንቱ በሰበታ ከተማ ላይ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ብቸኛው ተጫዋች ሆኗል ።

በአምስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ ሶስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 136 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። የ ባህር ዳር ከተማዎቹ ወሰኑ አሊ እና ምንይሉ ወንድሙ በሳምንቱ የቀይ ካርድ የተመለኩ ብቸኞቹ ተጫዋቾች ናቸው ። በሳምንቱ እየታዩ ከሚገኙት የማስጠንቀቂያ ካርዶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከስፖርታዊ ጨዋነት / አድራጎት ውጪ በመሆን ሲሆን በዚህ ሳምንትም አስራ አራት ተጫዋቾች በዚህ የተነሳ ለመመልከት ችለዋል ።

በአምስተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና 9.75 ነጥብ በማምጣት የዚህ ሳምንት ስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል ።

በሳምቱ ከተላለፉ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መካከል የቀይ ካርድ መመልከት የቻሉት ወሰኑ አሊ እና ምንይሉ ወንድሙ የአንድ ጨዋታ ቅጣት ሲተላለፍባቸው ክለቡ በጨዋታው አምስት ቢጫ ካርዶችን መመልከቱን ተከትሎ የ 5,000 ብር የገንዘብ መቆጮ ተላልፎባቸዋል ።

የውድድር ስነ – ስርዓት ኮሚቴው በአንክሮ ማሳሰቢያው እንዳስታወቀው የድሬድዋ ከተማው ዋና አሰልጣኝ ፍሰሐ ፆመልሳን በተለያዩ ቀናቶች በሰጧቸው የድህረ ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ በነገው እለት ከቀኑ 7:00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ፅ/ቤት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል ።

ፍሰሀ ፆመልሳን ኮቪድን አስመልክተው ” ኮቪድን የተመለከተ የምሰጠው ሀሳብ አለኝ ፣ ወላይታ ድቻን ለመውቀስ አይደለም።

ይሄ የህይወት ጉዳይ ነው ፣ ተመርምረን እንመጣለን ። የተመረመርንበት ወረቀት እና ቴሴራ ሊተያይ ይገባል።

ዛሬ አሁን ቼክ ስናደርግ ከእነሱ ሁለት ያልተመረመረ አግኝተናል። እንዲህ ዓይነት ችግር ስላለ አወዳዳሪው አካል ጥንቃቄ ቢያደርግ ጥሩ ነው ፤ የህይወት ጉዳይ ስለሆነ ” ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል ።

ከድሬደዋ በተጨማሪም የፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የቡድን መሪዎች እና የደጋፊዎች ማህበር ጥሪ ሲቀርብ በተለይም በሁለቱ ቡድኖች ዙሪያ በተፈጠረው የዲሲፕሊን ግድፈት ዙሪያ በነገው እለት ከ 7:30 ጅምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዕ/ቤት በመገኘት ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቃቸው ይፋ ሆኗል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor