በኮቪድ ክፉኛ የታመሰው የሲዳማ ቡናና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ምሽት 1:00 ይካሄዳል

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ ክለቦች በኮቪድ መጠቃታቸው በተለያየ ጊዜ ሲዘገብ ቢደመጥም እንደ ሲዳማና አዳማ የኮቪድ ወረርሽኝ ዜና የገነነባቸው ክለቦች አልታዩም።

ከትናንት በስቲያ በተደረገ የኮቪድ ምርመራ ከሁለቱም ክለቦች ከ31 ተጫዋቾች በላይ የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸዋል በመባሉ ዛሬ ምሽት 1:00 ሠዓት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ጨዋታ ላይካሄድ ይችላል አሊያም አነስተኛ ተጫዋቾች የተያዙበት ክለብ በፎርፌ አሸናፊ ይሆናል የሚሉ የተለያዩ መረጃዎች ሲወጡ ቆይተው ነበር።
አሁን መጨረሻ ላይ በተገኘ ዜና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የማይሰረዝ ና ፎርፌ የማይሰጥ ከመሆኑም በላይ ውድድሩ በወጣለት መርሀ ግብር መሠረት የሚካሄድ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከ32 የቡድኑ አባላት 27ቱ በኮቪድ ተጠቅተውበታል የተባለው ሲዳማ ቡናና በ21 ተጫዋቾቹ ላይ ተመሳሳይ የኮቪድ ምልክት ታይቶባቸዋል የተባሉት የአዳማ ከተማ አመራሮች በምርመራ ውጤቱ ዕምነት የለንም የሚል አቋም በማንፀባረቅ ትናንት ማምሻውን በድጋሚ ምርመራ እስከማድረግ ተገደው ነበር።

የሁለቱ ክለቦች የምርመራ ውጤት እስከ ዛሬ ስምንት ሠዓት ይገለፃል ተብሎ ሲጠበቅ ቆይቶ በመጨረሻ በመጣው የምርመራ ውጤት 27 አባላቱ ተይዘውበታል የተባለው ሲዳማ ቡና በመጨረሻ ሶስት ሠው ብቻ በቫይረሱ እንደተያዙበት የተረጋገጠ ሲሆን አዳማ ከተማ በበኩሉከ18 ተጫዋቾች 10ሩ ነፃ መሆናቸውን በድጋሚው የምርመራ ውጤት ተረጋግጧል።
በዚህም መሠረት የኮቪድ መጥፎ ጥላ ያጠላበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በተያዘለት ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተረገግጧል።በዚህም መሠረት የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ወደ ስታዲየም ደርሰዋል።

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.