የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ካሳለፍነው ሀሙስ ( 30/3/14 ) እስከ እሁድ ( 3/4/14 ) ድረስ መካሄዳቸውን ይታወሳል ።
በሳምንቱ በተደረጉ ስምንት ያህል ጨዋታዎች 17 ግቦች የተመዘገቡ ሲሆን በጨዋታዎቹ ላይም 29 የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርድ እና ሁለት የቀይ ካርዶችም ተመዝግበዋል ።
የኢትዮጵያ ፕራምየር ሊግ ውድድር አመራር እና ስነ ስርአት ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት በተፈጠሩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል ። የቀይ ካርድ የተመለከቱት ዳዊት ማሞ( መከላከያ ) እና በረከት ሳሙኤል ( ሰበታ ከተማ ) የአንድ ጨዋታ ቅጣት ሲተላለፍባቸው ወልቂጤ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ላይ የወልቂጤ ከተማ ቡድን መሪ መገኘት ከሚጠበቅባቸው 28 ያሀል ደቂቃዎችን ዘግይተው በመድረሳቸው የ 1,000 / አንድ ሺህ / ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል ።
ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር በነበረው የ 7ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የክለቡን አሰልጣኝንና ፣ የዕለቱን የጨዋታ አመራሮች በተደጋጋሚ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ፣ የክለቡ አስተባባሪዎች የክለባቸው ተጫዋቾች ጨዋታቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከተጫዋቾችና ከቡድን አመራሮች ጋር ግጭት ስለመፍጠራቸው ፣ የስታድየሙ ንብረት የሆኑትን ወንበሮች ስለመነቃቀላቸውና መስታወት በድንጋይ ስለመስበራቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ።
የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱና ከዚህ በፊት የፈፀሙትን ተደጋጋሚ ጥፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር የ150 000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍልና ከለቡ የሚያደርጋችውን 3/ሶስት/ ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑ ባለሜዳ ሆኖ ሲጫወት(ከወላይታ ዲቻ እና ከባህርዳር ከተማ) በዝግ ስታድየም እንዲሁም ከሜዳው ውጭ (ከመከላከያ) ሲጫወት ካለ ደጋፊው እንዲጫወት ከዚህም በተጨማሪ በሪፖርት ላይ የቀረቡትን የተነቃቀሉና የተሰበሩ ንብረቶችን እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ አስልቶ በሚያቀርበውን ዋጋ መሰረት ክፍያ እንዲፈፀም ተወስኗል ።
አስተያየት ይስጡ