መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል

አጋራ
አጋራ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 በ28ኛ ሳምንት በየተደረጉ 8 ጨዋታዎች ላይ 17 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ሲቆጠሩ 39 ቢጫ ካርድ በተጫዋቾች ላይ ተመዘዋል ፥ በሳምንቱ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ሰኔ 18 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ፍሪምፖንግ ሜንሱ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሪችሞንድ ኦዶንጐ(አዲስ አበባ ከተማ)፣ ፍሬው ጌታሁን(ድሬደዋ ከተማ) ፣ ክሌመንት ቦዬ(መከላከያ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቾቹም ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ ሲወሰን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ(ድሬዳዋ ከተማ) ክለቡ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኃላ የድህረ ጨዋታ ቃለመጠይቅ አለመስጠታቸው ሪፓርት የተደረገባቸው ለፈፀሙት ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል::

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...