በአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ እየተወዳደሩ እሚገኙት ባህርዳር ከተማዎች የተከላካይ አማካዩን ሀይማኖት ወርቁን አስፈርመዋል።
በትውልድ ከተማው ባህርዳር ከተማ ቡድን ኳስን በመጫወት የጀመረው የተከላካይ አማካዩ ሀይማኖት ወርቁ ለአውስኮድ ፤ አዲስአበባ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ድ ቻ ፣ ደቡብ ፖሊስ መጫወት ሲችል ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ለውልዋሎ አዲግራት ለመጫወት ፊርማውን ቢያኖርም በሰሜኑ ክፍል ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከክለቡ ጋር በመለያየት በአሰልጣኝ አብርሐም መብርህቱ የሚመራው የቀድሞ ቡዱኑን ባህርዳር ከተማን መቀላቀል ችሏል።
በ2010 ዓ.ም በአሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ ስር ወላይታ ድቻ በፕሪምየር ሊጉ እና በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ ቡድኑ ስኬታማ ጉዞን እንዲያደርግ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱ እሚታወስ ነው።
አስተያየት ይስጡ