በረከት ጥጋቡ በባሕር ዳር ከነማ የሚያቆየውን ውል ለማደስ ተስማምቷል ።
ከጣና ባሕር ዳር የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወቱ በቀጣይ መከላከያ ተስፋ ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በከፍተኛ ሊግ ለኢኮስኮ በመጫወት በቀጣይ ለወልቂጤ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ ተጫውቷል።
ከአራት ዓመት በፊት የጣና ሞገዶቹን የተቀላቀለው እና ሁለቱ የቡድኑ አንበሎች በቡድኑ በማይኖርበት ወቅት አርም ባንዱን አጥልቆ የተመለከትነው በረከት ጥጋቡ ለቀጣይ ዓመታት በባሕር ዳር ከነማ ለመቆየት የሚያስችለውን ውል አራዝሟል።