መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተደርገዋል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስባህርዳር ከተማአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫአዳማ ከተማዜናዎችፋሲል ከነማ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ተደርገዋል ።

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ የተገናኙት ከምድብ መውደቁን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ እና በምድቡ 1 ነጥብ የያዘው ፋሲል ከተማ ያደረጉት ነበር ። ጨዋታው በሁለቱም በኩል ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴን በማሳየት የጀመረ ነበር ።

አዳማም ሆነ ፋሲል በፍጥነት ወደ ጎል ለመድረስ ሲሞክሩም ተስተውሏል ። ጨዋታው ከተጀመረ ገና በ3ኛው ደቂቃ ፋሲል ከተማ ያገኘውን ቅጣት ምት የቀድሞ የአዳማ ከተማ ተጫዋች በረከት ደስታ በግሩም ሁኔታ አስቆጠረ ። ከጎሏ መቆጠር በኋላ አዳማ ከተማዎች የአቻነቷን ግብ ለማግኘት የፈጀባቸው ጊዜ 3ደቂቃ ብቻ ነበር በ6ኛው ደቂቃ ላይ ፋሲል ከተማዎች በግብ ክልላቸው አካባቢ ሲቀባበሉ የአዳማው አምበል ዳዋ ሆቴሳ ቀምቶ ለአቡበከር ወንድሙ አቀብሎት አቡበከር አስቆጥሮ ጨዋታው በ 1 ለ 1 ውጤት ቀጠለ ።

አዳማ ከተማዎች ኳሱን ተቆጣጥረው ተጭነው በመጫወት ጎል ለማስቆጠር ጥረት አድርገዋል ፋሲል ከተማዎችም የሚገኙ ኳሶችን ከኋላ መስርተው ለመውጣት ሲያደርጉ የነበረው ሙከራ በቀላሉ በአዳማ ከተማዎች ይከሽፍ ነበር ። በጨዋታው ለአዳማ የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረው አቡበከር ወንድሙ 37ኛ ደቂቃ ላይ በቀኝ ክንፍ በፍጥነት በመሄድ ለዳዋ ሆቴሳ ሊያቀብለው ሲሞክር ከድር ኩሊባሊ ጨርፎት በራሱ ጎል ላይ አስቆጠረ ።

አዳማ ከተማም መሪነቱን ወደ 2 – 0 ማስፋት ቻለ ። የመጀመሪያው አጋማሽም በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ ። በሁለተኛው አጋማሽ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን ፋሲል ከነማ ሁለት ቅያሪዎችን በማድረግ ነበር የጀመሩት ።

ጨዋታው በፈጣን እንቅስቃሴ የቀጠለ ሲሆን ሁለቱም ግብ ለማስቆጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል ። 64ኛው ደቂቃ ላይም ለአዳማ ከተማ የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረው እና ለሁለተኛዋም ግብ መንስኤ የነበረው አቡበከር ወንድሙ በቀኝ ክንፍ ይዞት የሄደውን ኳስ ለአሜ መሀመድ አቀብሎት አሜም የአዳማን 3ኛ ግብ ማስቆጠር ቻለ ።

አዳማ ከተማ መምራታቸውን ተከትሎ በከፍተኛ የራስ መተማመን ጥሩ ጨዋታ በመጫወት ወደ ፊት ሄደው ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን በማድረግ ቀጥለው በ81ኛ ደቂቃ ላይ አሜ መሀመድ በድጋሚ አስቆጥሮ አዳማ ከተማዎች 4 ለ 1 መሩ ። ፋሲል ከነማዎች ግቦችን ለማስቆጠር በፊት መስመር በሚገኘው ኦኪኪ አፎላቢ አማካይነት ወደ ግብ ለመድረስ ቢሞክሩም በአዳማ ከተማ ተከላካዮች ሊከሽፉ ችለዋል ።

ሁለቱም ክለቦች ተጨማሪ ግብ ሳያስቆጥሩ የመሀል ዳኛው የጨዋታ ማጠናቀቂያ ፊሽካ ድምፅ ተሰማ ። በዚህም በባህር ዳር እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ የተመሰረተ የማለፍ ዕድልን ይዞ የገባው ፋሲል ከነማ መውደቁን አረጋገጠ ። በጨዋታው አንድ ጎል አስቆጥሮ ለሁለት ጎሎች መቆጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው አቡበከር ወንድሙ የጨዋታው ኮከብ በመባል የዋንጫ እና የ12,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል ።

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ቀድሞ ማለፉን ያረጋገጠውን ቅዱስ ጊዮርጊስን እና በ8 ሰአቱ ውጤት መሰረት ማለፉን ያረጋገጠውን ባህርዳር ከተማን ያገናኘ ነበር ። ጨዋታው እንደተጀመረ ገና 1 ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ የቅዱስ ጊዮርጊሱ 9 ቁጥር ለባሽ ፀጋዬ መላኩ የመጀመሪያውን ጎል ለቅዱስ ጊዮርጊስ አስቆጠረ ። ከግቧ መቆጠር በኋላ ባህርዳሮች ኳሱን ተቆጣጥረው የተጫወቱ ሲሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል የባህርዳርን የኳስ ፍሰት በማቋረጥ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ጎል ለማስቆጠር ጥረት አድርገዋል ። 26ኛ ደቂቃ ላይ በቡልቻ ሹራ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን ቅጣት ምት አምበሉ ሀይደር ሸረፋ ሲያሻማው ተከላካዩ ፍሪምፖንግ ሜንሱ ደግሞ ኳሷን ከመረብ አዋሀዳት የቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነትም ወደ 2 ለ 0 ተሸጋገረ ።

ባህርዳሮች ግልፅ የማግባት ዕድሎችን ቢያገኙም በቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ባህሩ ተመልሰውባቸዋል ። በጨዋታው 40ኛ ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ግብ ለፈረሰኞቹ ያስቆጠረው ፀጋዬ መላኩ ከባህርዳር ተከላካይ የነጠቀውን ኳስ በግሩም አጨራረስ ለክለቡ 3ኛ ለራሱ ደግሞ 2ኛ ግብ አስቆጠረ ። የመጀመሪያው አጋማሽም በቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።

የጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽም ከጅማሮው ፈጣን የነበረ ሲሆን የጣና ሞገዶቹ ኳሱን ተቆጣጥረው ብልጫ በመውሰድ ጎል ለማስቆጠር ቢጥሩም ከፊት መስመር ላይ የነበረው ድክመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች ጥንካሬ ጋር ተዳምሮ ሳይሳካላቸው ቀርቷል ።

ሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ከሁለቱም በኩል እንደ መጀመሪያው አጋማሽ በጎል ሙከራዎች የታጀበ አልነበረም ። ሌላ ተጨማሪ ጎል ሳይታከል ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ። በጨዋታው ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው ፀጋዬ መላኩ የጨዋታው ኮከብ በመባል የዋንጫ እና የ12,000 ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል ።

በዚህም መሰረት ምድብ ለን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስቱንም ጨዋታ በማሸነፍ በ9 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ባህርዳር ከተማ በ4 ነጥብ ሁለተኛ በመሆን ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል ። በተጨማሪም አዳማ ከተማ በ3 ነጥብ እንዲሁም ፋሲል ከተማ በ1 ነጥብ የሶስተኛ እና የአራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል ።

የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ረቡዕ ዕለት የሚደረጉ ሲሆን በ8 ሰአት ጅማ አባጅፋር ከ ባህርዳር ከተማ አንዲሁም በ10 ሰአት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ ይጫወታሉ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...