15ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ ሲጀመር የመክፈቻውን ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከጅማ አባጅፋር ያደርጋሉ።
የደቡብ ሱዳኑ ክለብ ሙኒኪ ባለመምጣቱ የአሸናፊ በቀለ ጅማ አባጅፋር እንዲተካው ተደርጎ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ጠንካራ ጨዋታ ያደርጋሉ ። የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ኮከቦቹ ዳዊት እስጢፋኖስና መስዑድ መሃመድ የቀድሞ ክለባቸውን የመግጠም እድል አግኝተዋል።
ሲቲ ካፑ ሰኞ ሲቀጥል ከቀኑ 8 ሰአት አዲስ አዳጊዎቹ አዲስ አበባ ከተማ ከመከላከያ በ10 ሰአት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ ። ሁለቱ ጠንካራ ተቀናቃኞች መገናኘታቸው ውድድሩን ከጅማሮው ደማቅ አድርጎታል።
- ማሰታውቂያ -
በክለቦች ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የተስተካከለው መርሃግብር…
ቅዳሜ
8 ሰአት
አዲስ አበባ ከመከላከያ
10ሰአት
ኢት.ቡና ከጅማ አባጅፋር
ሰኞ በ8ሰአት
ባህርዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ
በ10 ሰአት
ቅ/ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ
ረቡዕ
ከቀኑ8 ሰአት
አዲስ አበባ ከተማ ከጅማ አባጅፋር
ከቀኑ 10 ሰአት
ኢት.ቡና ከመከላከያ
ሃሙስ
ከቀኑ 8 ሰአት
ባህርዳር ከፋሲል ከነማ
ከቀኑ 10 ሰአት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ
ቅዳሜ በ8ሰአት
መከላከያ ከጅማ አባጅፋር
በ10ሰአት
ኢትዮጵያ ቡና ከ አዲስ አበባ ከተማ
እሁድ
በ8 ሰአት
አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ
በ10 ሰአት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህርዳር ከተማ