በምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታ ቀን 8:00 ሰዓት ላይ አስቀድመው መዉደቃቸዉን ያረጋገጡት አዳማ ከተማዎች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ለማለፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከሚያስፈልጋቸው ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታቸውን በአበበ በቂላ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።
አፄዎቹ ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ለማለፍ ጨዋታውን የግድ ማሸነፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ምንም እንኳን አዳማ ከተማን ቢያሸንፉ ባህርዳር ከተማ ከተጋጣሚው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ የሚጋራ ወይም የሚያሸንፍ ከሆነ አፄዎቹ ከ15ኛዉ አዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ዉጭ የሚሆኑ ይሆናል።
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ አስቀድመው ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ማለፋቸን ያረጋገጡት ፈረሰኞቹ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ሲሆን የጣና ሞገዶቹ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመቀላቀል ከጨዋታዉ አንድ ነጥብ በቂያቸዉ ሲሆን በአንፃሩ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ነጥብ የሚጥል ከሆነ ባህርዳር ከተማዎች በየትኛውም ዉጤት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚቀላቀሉ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ