በአቤኔዘር አበበ
ኢትዮጵያ ቡና ከሀላባ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በ1-1 ነጥብ መጋራት ተጠናቋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተመልካች የሚስብ እንቅስቃሴ ሳያሳዩ የ45 ደቂቃዎችን አጠናቀዋል። በሁለቱም በኩል ግብ ጠባቂዎችን የሚፈትን ሙከራ ሳይደረግ የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 ተጠናቋል።
ከዕረፍት መልስ በኋላ ግን ሁለቱም ቡድኖች የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት የተሻለ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና የጨዋታ ብልጫውን ወስዶ ነበር።ኢትዮጵያ ቡና በ49ኛው ደቂቃ ዘላለም አባቴ አመቻችቶ ያቀበላትን ኳስ ኮስታይባ ምቦኑዩምዋሚ በግባሩ በመግጨት ኳሱን መረብ ላይ አሳርፎ ቡድኑን መሪ አድርጎ ነበር።የቡና መሪነት ግን ለረጅም ጊዜ አልቆየም። በ55ኛው ደቂቃ ረጅብ ሚፍታህ በሀላባ ከተማ ተጫዋች እስራኤል ሾጎለ ላይ በፈጸመው ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሽመክት ጉግሳ ወደ ግብነት በመቀየር ሀላባ ከተማን አቻ አድርጓል።በቀሪው የጨዋታ ጊዜ ሌላ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በ1-1 ውጤት ተጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ