በአቤኔዘር አበበ
በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1-1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ባህርዳር ከተማ የጨዋታ ብልጫውን በመውሰድ ተጫውተዋል። ሆኖም የፈጠሩትን አጋጣሚዎች ወደ ግብ መቀየር አልቻሉም። ወልዋሎ አዲግራት ዩ. በበኩሉ ያገኙትንአጋጣሚ በአግባቡ ተጠቅሞ በ39ኛው ደቂቃ በየነ ባንጃ ከሳጥን ውጭ አክርሮ በመምታት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ አድርጎታል። የመጀመሪያው አጋማሽም በወልዋሎ አዲግራት ዩ. መሪነት ተጠናቋል።
ከዕረፍት መልስ ባህርዳር ከተማ በተሻለ አጀማመር ወደ ሜዳ ተመልሳ በ50ኛው ደቂቃ ስምኦን ማሩ በሽመልስ በቀለ ላይ በፈጸመው ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት አንተነህ ተፈራ ወደ ግብ በመቀየር የጨዋታውን ውጤት 1-1 አድርጎታል።ከአቻነቱ ግብ በኋላ ባህርዳር ከተማ ጫናውን በማሳደግ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ብጥሩም የወልዋሎ አዲግራት ዩ. መከላከል መስበር አልቻለችም። ወልዋሎም ከአቻነቱ ግብ በኋላ የጨዋታውን ብልጫ ተወስዶበት በተጨማሪ የሚጠቅም አጋጣሚ ሳይፈጥር ጨዋታውን ጨርሷል።ባህርዳር ከተማ 1-1 ወልዋሎ አዲግራት ዩ.
አስተያየት ይስጡ