የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ያሬድ ብሩክ (ነገሌ አርሲ) : ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ 5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ9ዐ+3ኛ ደቂቃ ላይ ሆን ብሎ የተጋጣሚ ቡድንን ተጫዋች በክርን በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ኮነህ ጄግባይ (መቻል): ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ 5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ62ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ሃዋሳ ከተማ ክለቡ ከጋሞ ጨንቻ ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- በረከት ደስታ
- ቹኩውብኳ አንቶኒ
- እስራኤል ሰማያት
- ዳግም ተፈራ
- ፈቃደስላሴ ደሳለኝ
- ንጋቱ ገ/ስላሴ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/
እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
4. ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አሚኑ ነስሩ
- ሻሂዱ ሙስጠፋ
- ቢላል ገመዳ
- ሀብታሙ ጉልላት
- ናትናኤል ዳንኤል
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
5. ሀላባ ከተማ ክለብ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ተጋጣሚው ቡድን ደጋፊዎች ሀይላንድ መወርወላቸውን፣ እንዲሁም በ55ኛው ደቂቃ የብሎኬት ስብርባሪዎችንና ድንጋይ በመወርወር ደጋፊዎችን ማፈንከታቸውን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ደጋፊዎቹ ለፈጸሙት ጥፋት እንዲሁም በአስተናጋጅነት ወቅት ችግሮች እንዳይከሰቱ የማድረግ ሙሉ ኃላፊነት የሚጠየቅ በመሆኑ፣ በኢ.እ.ፌ. የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀጽ 66 ተራ ቁጥር 3(ሀ) መሠረት ብር 75,ዐዐዐ (ሰባ አምስት ሺህ) እንዲከፍል ወስኗል።
6. ሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ከሀላባ ከተማ ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ተጋጣሚው ቡድን ደጋፊዎች ሀይላንድ መወርወራቸውን፣ በ55ኛው ደቂቃ በተጋጣሚው ቡድን ደጋፊዎች ላይ የተወረወሩባቸውን የብሎኬት ስብርባሪዎችና ድንጋይ በመመለስ እነሱም ቁሳቁሶችን በመወርወር ምላሽ መስጠታቸውን፣ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ወደ ቀኝ ጥላ ፎቅ(የሞላ) ለመግባት ጥረት ያደርጉ የነበሩት ብዛት ያላቸው ደጋፊዎች በቦታው የነበሩትን የፀጥታ አካላት ትዕዛዝ ላለመፈጸም ከፍተኛ ሁከትና ግርግር|ረብሻ መፍጠራቸውን ፣ አንዳንዶቹም አጥር ዘለው ስለመግባታቸውን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ደጋፊዎቹ ለፈጸሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ. የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 አንቀጽ 66 ተራ ቁጥር 3(ሀ) መሠረት ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) እንዲከፍል ወስኗል።
7. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት፣ በእረፍት ሰዓት በዕለቱ ያልተመዘገበ አንድ ተጫዋች ወደ ክለቡ መልበሻ ክፍል መግባቱን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት በ2019 በተሻሻለው የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 13.2 በተራ ቁጥር 4 መሠረት ብር 25000/ሀያ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
አስተያየት ይስጡ