በአቤኔዘር አበበ
መቻል ኢትዮጵያ መድንን አሸንፎ የሊጉን መሪነት ተረከበ!

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ መድንን 3–1 በማሸነፍ ሙሉ ሦስት ነጥብ አግኝቷል።በጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ኢትዮጵያ መድን በአጨራረስ ድክመት ሲቸገር፣ መቻል የጨዋታውን ብልጫ በመውሰድ በ10ኛው ደቂቃ መሪነቱን ያዘ። መሐመድ አበራ በሳጥን ውስጥ ያቀበለውን ኳስ ቸርነት ጉግሳ በግብነት በመቀየር መቻልን ወደ መሪነት አሸጋገረ። የመጀመሪያውም አጋማሽ በመቻል 1–0 መሪነት ተጠናቀቀ።ከዕረፍት መልስም መቻል የጨዋታውን ብልጫ በማስቀጠል በ58ኛው ደቂቃ የኢትዮጵያ መድን ተጫዋች እንዳለ ዮሐንስ በኮንህ ጄግበይ ላይ በተሠራ ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ፈቱዲን ጀማል ወደ ግብነት በመቀየር የመቻልን መሪነት ወደ 2–0 አሳደገ።በ90ኛው ደቂቃ መሐመድ አበራ ለመቻል ሦስተኛውን ግብ በማስቆጠር የድሉን ርግጠኝነት አጠናከረ። በጭማሪ ደቂቃ 90+4 አማኑኤል ኦሊሳ ለኢትዮጵያ መድን አንድ ግብ ቢያስቆጥርም፣ ቡድኑን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም።በዚህም መቻል 3–1 በሆነ ውጤት ድል በማድረግ በአራተኛው ሳምንት የሊጉን ሦስት ነጥብ ማሳካት ችሏል።
አስተያየት ይስጡ