በአቤኔዘር አበበ
ጋሞ ጨንቻ የመጀመሪያ አንድ ነጥብ አሳካ!

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት የሦስተኛ ቀን ጨዋታ ጋሞ ጨንቻና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-0 በሆነ ውጤት አቻ ተለያዩ።በመጀመሪያው አጋማሽ ጋሞ ጨንቻ የጨዋታ ብልጫ ወስዶ መጫወት ቢችልም ወደ ግብ መቀየር አልቻለም። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንፃሩ ደካማ እንቅስቃሴ ባሳየበት አጋማሽ ግብ ሳይቆጠር ተጠናቋል።ከዕረፍት መልስም ጋሞ ጨንቻ የመሀል ሜዳውን ብልጫ በመውሰድ የጨዋታውን ፍሰት መቆጣጠሩን ቢቀጥልም የንግድ ባንክን መከላከያ ጥሶ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።በመጨረሻም ሁለቱ ቡድኖች ያለ ግብ በመለያየት እያንዳንዳቸው አንድ ነጥብ ወሰዱ።የሙሉ ሰዓት ውጤትጋሞ ጨንቻ 0-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አስተያየት ይስጡ