የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ1 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጨዋች የሆኑት
- ፍፁም ጥላሁን
- ሲሞን ፒተር
- አቤል ማሙሽ
- ቅዱስ ዳዊት
- ተስፋዬ ታምራት
- ዴቪድ ኦፖንግ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/
እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
2. ሲዳማ ቡና ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ ዳኞች ግጥሚያውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያሉ፣ የክለቡ ደጋፊ ማህበር አመራሮችና አስተባባሪዎች እስከ ኮሪደሩ ድረስ በመምጣት እንደተሳደቧቸው ሪፖርት ቀርቦበታል።
ስለሆነም የክለቡ ደጋፊዎች ለፈጸሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ. የዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3፣ ምዕራፍ 3፣ አንቀጽ 66፣ በተራ ቁጥር 4(ሀ) መሠረት ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
3. ፋሲል ከነማ ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ግጥሚያ ከተወሰነለት ሰዓት በ3 ደቂቃ ዘግይቶ እንዲጀመር ምክንያት መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት ክለቡ በ2019 በተሻሻለው የውድድር ደንብ ክፍል 1፣ አንቀጽ 13፣ ንዑስ አንቀጽ 13.2፣ በተራ ቁጥር 19 እና 20 መሠረት ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
እንዲሁም በጨዋታው መዘግየት ምክንያት የቀጥታ ስርጭት መብት የወሰደው ድርጅት ለአክሲዮን ማህበሩ ካሳ እንዲከፈለው ከጠየቀ፣ አክሲዮን ማህበሩ የሚከፍለውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክለቡ እንዲሸፍን ወስኗል።
4. መቻል ክለቡ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት የቡድን ፎቶ አነሳስ ደንብን መጣሱን የሚገልጽ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት ክለቡ በ2019 በተሻሻለው የውድድር ደንብ ክፍል 1፣ አንቀጽ 13፣ ንዑስ አንቀጽ 13.2፣ በተራ ቁጥር 17 መሠረት ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
5. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት የእግር ኳስ ጨዋታ፣ በጥላ ፎቅና በካታንጋ ላይ የነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች 6 ወንበሮችን ከቦታቸው ነቅለው እንዳነሷቸውና 2 ወንበሮችን እንደሰበሩ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ክለቡ በአጠቃላይ የተነቀሉትንና የተሰበሩትን 8 ወንበሮች እንዲያሠራ ወይም የስታዲየሙ ባለቤት አሠርቶ የሚያቀርበውን ወጪ እንዲከፍል ወስኗል።
አስተያየት ይስጡ