የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው መቻል የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በ2018 የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ተብለው ይጠበቁ ከነበሩ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው መቻል በሚያስቆጭ መልኩ ይጥላቸው በነበሩ ነጥቦች የተነሳ አመቱን ከ38 ጨዋታዎቹ 14 በማሸነፍ በ15 ጨዋታዎች አቻ ወጥቾ በ9 ደግሞ በመሸነፍ 44 ጎሎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ በማሳረፍ 31 ደግሞ በራሱ ጎል ላይ ተቆጥሮ በ13 የግብ ክፍያ 57 ነጥቦችን ይዞ የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱ ቡድን ማጠናቀቅ ችሏል።
ከወራቶች በፊት በክረምቱ ለ2019የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በዋና ሲሳይ ከበደን በረዳት አሰልጣኝነት መቅጠር የቻለው ጦሩ በመቀጠል ዝውውሩን በመቀላቀል ከሀገር ውስጥ እና ውጪ 10 አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ ማድረግም ችሏል። ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉን ከአልናፍጥር ኢራቅ ፣ የግራ ተከላካዮቹን ረመዳን የሱፍ እና ያሬድ ካሳዬን እንዲሁም የቀኝ ተከላካዩ በረከት ካሌብን ከኢትዮጵያ መድን ፣ ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉን ከምድረገነት ሽረ እና እስከ አሉን ከክለቡ ጋር ልምምድ እየሰራ የማይገኘው አቡበከር ናስር ከደቡብ አፍሪካው ሰንዳውን እንዲሁም ከውጪ ጊኒያዊውን ግብ ጠባቂ መሐመድ ካራን ከጋናው አሻንቲ ኮቶኮ ፣ ላይቬሪያዊውን አማካይ ሙሪስ ኬኔህን እና ሱዳናዊውን ተከላካይ ከደቡብ ሱዳኑ ጃሙስ ክለብ እንዲሁም ደግሞ ደቡብ ሱዳናዊውን አጥቂ ቲቶ ኦኬሎ ከሊቢያው አልሳዳቃ ክለቡ ማስፈረም ችሏል።
እንዲሁም በተጨማሪ በክለቡ ውል ያራዘሙ ሁለት ቦታ በመፈረማቸው ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተው የነበሩት አብዱልከሪም ወርቁ እና ዓለምብርሀን ይግዛው ጨምሮ ዮሐንስ መንግሥቱ አማኑኤል ዮሀንስ፣ ዳዊት ማሞ እና ዮሐንስ ደረጄ ናቸው ።
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የአየር ሐይል የልምምድ ማዕከል ከነሐሴ 12/2018 ጀምሮ በጂም ፣ በሜዳ እና በክፍል የልምምድ ጊዜያቸውን ከፋፍለው ሲሰሩ የነበሩት መቻሎች በወዳጅነት ጨዋታ ሸገር ከተማን 5ለ2 እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ደግሞ 2ለ0 በማሸነፍ ከባህርዳር ከተማ እና ወልዋሎ ጋር በተመሳሳይ 2ለ2 ከፋሲል ከነማ ጋር 1ለ1 በወዳጅነት ጨዋታዎቻቸው ማስመዝገብ ችለዋል። የዝግጅት ጊዜያቸውን ያገባደዱት መቻሎች የፊታችን ዕሁድ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ መክፈቻቸውን ከሀዋሳ ከተማ ጋር በማድረግ ውድድራቸውን ይጀምራሉ።
አስተያየት ይስጡ