የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ባህርዳር ከተማ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከፍተኛ የአቻ ውጤትን በማስመዝገብ የባህርዳር ከተማን ያህል በሊጉ ያሳየን ክለብ አልነበረም። የወጥነት ችግሮችን በሊጉ ደጋግመን ያየንበት ክለቡ የተመለከትንበት ባህርዳር ከተማ በሊጉ ከተደረጉ 38 ጨዋታዎች በኋላ 9 በማሸነፍ 21 አቻ ውጤቶችን በማስመዝገብ 8 በመሸነፍ 28 ጎሎችን አስቆጥሮ በተመሳሳይ 28 ተቆጥሮበት 11ኛ ደረጃ ላይ ያለ ምንም የግብ ክፍያ በ48 ነጥቦች በመቀመጥ የ2018 የፕሪምየር ሊግ ቆይታውን መጫወት የቻለ ሲሆን ካለፉት ሁለት አመታት በመጠኑ ወረድ ካሉት ውጤቶቹ በይበልጥ ተሻሽሎ ለመገኘት ለ2019 የውድድር ዘመን አራት አመታትን በቡድኑ ውስጥ ያሳለፉትን አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን ኮንትራት በማራዘም ክረምቱን ቀዳሚ ስራዬ በማለት ነበር የጀመረው።
የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን ውል ባላቸው አንድ ነባር አመት ላይ የተጨማሪ ሁለት አመት ውልን በማከል ወደ ዝውውር ገበያው የገባው ቡድኑ አንጋፋውን አማካይ ሽመልስ በቀለን ከሀዋሳ ከተማ ፣ አጥቂው ኪቲካ ጅማን ከነገሌ አርሲ ፣ አጥቂው ብሩክ ሙሉጌታን ከኢትዮጵያ መድን ፣ ተከላካዩ አስራት ቱንጆን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ አማካዩ ኬኔዲ ገብረፃዲቅ ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ የግራ መስመር ተከላካዩ ዮዳሄ ዳዊትን ከመቻል ከከፍተኛ ሊጉ ደግሞ ግብ ጠባቂው እንዳሻው ሀብቴን ከደሴ ከተማ ፣ ግብ ጠባቂው ሐይደር ሙደሲርን ከአዲስ ከተማ እና አጥቂው ናትናኤል ጋቻፎን ከቦዲቲ ከተማ እንዲሁም የቀድሞው የድሬዳዋ እና የመቻል አጥቂ ዩጋንዳዊው ቻርለስ ሙሴጌን ክለቡ ያስፈረማቸው 10 አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ናቸው።
ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ ወንድሜነህ ደረጀ ፣ በረከት ጥጋቡ ፣ አንተነህ ተፈራ ፣ አደም አባስ ፣ ግርማ ዲሳሳ ፣ ማንያዘዋል ካሳ ፣ ብሩክ ሰሙ ፣ ትንሳኤ አዲሱ እና ሀይለስላሴ ልጁአለም ፣ ፍፁም ፍትህአለሙ ደግሞ ውላቸውን ያደሱ 10 ነባሮቹ ተጫዋቾች ሆነዋል።
በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እና በረዳቶቹ እየታገዘ በአዳማ ከተማ ከነሀሴ 10/2018 አንስቶ ልምምዳቸን ማድረግ የጀመሩት የጣና ሞገዶቹ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ በያዟቸው የልምምድ ምዕራፎቻቸው ታግዘው የስልጠና ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ በወዳጅነት ጨዋታ ደግሞ ራሳቸውን ፈትሸዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስን 1ለ0 ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2ለ1 ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3ለ2 ፣ ወልዋሎን 1ለ0 ሲያሸንፉ ከመቻል ጋር 2ለ2 እንዲሁም በኢትዮጵያ ቡና 2ለ1 ሽንፈት በማስተናገድ ዝግጅታቸውን ቋጭተው የፊታችን ዕሁድ ወደ ሆሳዕና ተጉዘው በአብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ባህርዳር ከተማን በመግጠም የሊግ ጉዟቸውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ