መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የክለቦች ዝግጅት | ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ቅዱስ ጊዮርጊስ

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ስሙን ከፍ በማድረግ ያስቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ1991 ጀምሮ በሊጉ በመሳተፍ 16 የሀገሪቱን የሊግ ዋንጫዎች ወደ ቋቱ በመክተት የሚስተካከለው የሀገራችን ክለብ አልተገኘም። ባለፉት ጥቂት አመታቶች ውስጥ በመሪዎቹ ለሁለት መከፈል በፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ለመግባት የተገደደው ቡድኑ ከለመደው የሊግ ጥንካሬውን ወረድ ብሎ በሊጉ ለመቀዛቀዝ የተገደደው መገደዱን ያስተዋልን ሲሆን በ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይም ይህ የፋይናንስ ቀውሱ ቀጥሎ በሜዳ ውጤቱ ላይ ጥላ ቢያጠላበትም የኋላ ኋላ ግን በአመራሮች ለውጥ የተነሳ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ተቋሞ ደራሽነት ክለቡ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ አጋፋሪነት በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾ አማካሪነት እንዲሁም በቡድኑ የአሰልጣኝ አባላት እና በአመራሩ የጋራ ትግግዝ ከነበረበት የወራጅ ቀጠናው ወጥቶ በ38 የሊግ ጨዋታው 14 አሸንፎ በዕኩሌታ 12 አቻ እና ሽንፈት አስተናግዶ 33 ጎሎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ በማሳረፍ 31 ጎሎችን በአንፃሩ በማስናገድ 2 የግብ ክፍያ ይዞ በ54 ነጥቦች 6ተኛ ደረጃን ይዞ አመቱን ለመቋጨትም በቅቷል።

ከብዙዎቹ አስቸጋሪ ወራቶች ማለፍ በኋላ ለያዝነው አመት በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ ከአልጄሪያው ክለብ ኤ ኤስ ስቲፍ ጋር በመለያየት ቅዱስ ጊዮርጊስን በአማካሪነት ሲመሩ የነበሩትን የቀድሞው አሰልጣኙ ሰርቪያዊውን ሰው ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾን ለቀጣዮቹ አምስት አመታት በዋና አሰልጣኝነት መንበር ከሌሎች ሀላፊነቶች ጋር በመሾም አንጋፋውን አሰልጣኝ ስዩም ከበደን ደግሞ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ከውጪ ሀገር ረዳት አሰልጣኝ እንደማያመጣ የታወቀው ቡድኑ ቤልጂማዊውን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ራዴ ሞዬቪችን ከነባሮቹ የሀገር ውስጥ ረዳቶቹ ሳምሶን ሙሉጌታ እና አዳነ ግርማን በጋራ በመያዝ በዝውውሩ በመሳተፍ አዳዲስ ተጫዋቾችን በመቀላቀል ወደ ዝግጅት ምዕራፍ አምርቷል።

ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾችን ስንመለከት የመስመር አጥቂዎቹን ተመስገን ብርሀኑ እና ፀጋአብ ግዛውን ከሀድያ ሆሳዕና ፣ አማካዩ ብሩክ እንዳለን ከወልዋሎ ፣ አጥቂው ናትናኤል ዳንኤልን ከንግድ ባንክ ፣ የግራ ተከላካዩ ያሬድ የማነን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ አጥቂው አማኑኤል ኤርቦን ከኢትዮጵያ መድን ለሁለተኛ ጊዜ ሲያስፈርም ፣ ተከላካዩ ቢኒያም በቀለን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ አማካዩ ብሩክ በላቸውን ከኢትዮጵያ መድን ፣ ፣ ግብ ጠባቂዎቹ ቢኒያም ገነቱን ከወላይታ ድቻ እና ፂሆን መርዕድን ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ከከፍተኛ ሊጉ ደሴ ከተማ ቢላል ገመዳን ክለቡ በይፋ ከሀገር ውስጥ ሲቀላቅል ባለፈው አመት አጋማሽ ፈርሞ ክለቡ በነበረበት ዕግድ ምክንያት መጫወት ያልቻለውን ዲሞክራቲክ ኮንጓዊውን አጥቂ ክሪስ ቶሉንጋን ከአልጄሪያው ፓራዱ ክለብ መቀላቀል የቻላቸው አስራ አንዱ አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ሲሆኑ በአንፃሩ እንደ ኬኒያዊው ግብ ጠባቂ ፋሩክ ሻኪሎ ፣ ብርሀኑ አሻሞ ፣ ተገኑ ተሾመ እና አበባየው ዮሐንስን ጨምሮ በድምሩ ወደ ስምንት ከሚደርሱ ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል።

በሌላ በኩል ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ እነሰደ ፉአድ አብደላ ፣ ብሩክ ታረቀኝ ፣ ፀጋ ከድር ፣ ኮክ ኩዌት ፣ አሚኑ ነስሩ እና ፋኑኤል አዳሙ አይነት ነባር ተጫዋቾች ደግሞ ውላቸው የታደሰላቸው ሲሆን በቀጣይም ወጣቶችን ከታችኛው ቡድን ለማሳደግ ክለቡ በመመልከት ላይ እንዳለ ሀገሬ ቴሌቪዥን በሰበሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ ችሏል።

ከነሀሴ 13/2018 ጀምሮ ቢሾፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ውስጥ በቀን ሦስቴ ፣ ሁለቴ እና በመጨረሻም አንድ ጊዜ በጂም እና በሜዳ ተግባራት የቅድመ ውድድር ዝግጅትን በመስራት ያሳለፉት ፈረሰኞቹ በአሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾ የገነቡትን ቡድን ለመገምገም ከየትኛውም የሊጉ ክለቦች በላይ የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ ዝግጅታቸውን በማገባደድ ለሊጉ ውድድር ራሳቸውን አዘጋጅተዋል።

ባደረጓቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ለ2 እና በባህርዳር ከተማ 1ለ0 ሲሸነፉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር 1ለ1 ፣ ወልዋሎን 3ለ1 እና የጋምቤላውን የስብስብ ቡድን ባሮን 5ለ0 ሲያሸንፉ ከሀገር ውጪ ወደ ታንዛኒያ አምርተው ደግሞ በታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ 1ለ0 እና በኮንጎው ሞኒማ ዩኒየን ክለብ 2ለ0 በመሸነፍ ራሳቸው በወዳጅነት ጨዋታ ለማየት ጥረት አድርገዋል። የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በጀመረበት በማግስቱ መስከረም 30/2019 ነገሌ አርሲን በአዲስ አበባ ስታዲየም ክለቡ በመግጠም ወደ ውድድር የሚገባም ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...