የ2019 የውድድር ዘመን ሊጀመር ጥቂት ቀናት በቀሩት በዚህ ወቅት፣ ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት ተስፈኛ የቀድሞ የወጣት ቡድን ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል።

በቅርቡ በተካሄደው የያሆዴ ካፕ ውድድር ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ የብዙዎችን ትኩረት የሳቡት ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ዳግም ደሳለኝ እና የቀኝ መስመር ተከላካይ ተጫዋቹ ሄኖክ ደሳለኝ (ቱላ) በዋና አሰልጣኛችን ሳምሶን አየለ ተመርጠው የሀዲያ ሆሳዕና ዋናው ቡድን አካል ሆነዋል።
ሁለቱም ተስፋ ሰጪ ተጫዋቾች በሀዲያ ሆሳዕና የሚያቆያቸውን የአንድ ዓመት የኮንትራት ውል በይፋ ፈርመዋል።
አስተያየት ይስጡ