ብሩንዲያዊው የመሐል ዳኛ የሲዳማ ቡና እና አልሂላል ኦምዱርማንን ጨዋታ ይመራዋል።

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛው ዙር የማጣሪያ መርሀግብር ከቀጣዩ ወር መግቢያ ቀናቶች ጀምሮ መደረጋቸውን ይጀምራሉ። ኢትዮጵያን በመወከል እየተካፈለ የሚገኘው ሲዳማ ቡና በመጀመሪያው ማጣሪያ የቻዱን ክለብ ኤግሎንስ በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ማጣሪያም ጥቅምት 8/2019 ዕሁድ 10 ሰዓት ሲል የብሩንዲውን ክለብ ኤይግል ኖይር ማካንባን አሸንፎ ካለፈው የሱዳኑ አልሂላል ኦምዱርማን ጋር በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታል።
ይህንንም የድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታ የብሩንዲ ዝግነት ያለው
የ41 አሙ ፓስፊኩዊ ንዳቢሀዌኒማና እንዲመራው ካፍ መርጦታል። በእኛ አቆጣጠር በ2018 የካቲት ወር ላይ የግብፁ አልመስሪ ከዛምቢያው ዜስኮ ዩናይትድ ጋር ካደረጉት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከወራቶች በኋላ ዳኛው ይህንን ጨዋታ ይመራል።
አስተያየት ይስጡ