በአዲሱ አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ መሪነት ዝግጅታቸውን በሀላባ ስታዲየም በማከናወን ላይ የሚገኙት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች ሁለት ተጫዋቾችን የግላቸው ሲያደርጉ ከአንድ ተጫዋች ጋር መለያየት ችለዋል።

በወልቂጤ ከተማ እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ በደብረብርሃን ከተማ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው ሀይደር ሽኩር በመንጌ ቤንሻንጉል የከፍተኛ ሊግ ቆይታን ያደረገው ሲራጅ ከድር ሀላባ ከተማን በይፋ መቀላቀል ችለዋል።
ሀላባ ከተማ ውሉን አራዝሞለት ከነበረው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ብሩክ ቦጋለ ጋር መለያየቱም ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ