ቤኒናዊው አማካይ ሮማሪክ አሞውሱ ወደ ፋሲል አምርቷል።
ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ በማከናወን ላይ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች የቤኒን ዜግነት ያለውን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሆኖ መጫወት የሚችለው ሮማሪክ ዲንሆ አሞውሱ አስፈርመዋል።
በቤኒን ኮተን ስፖርት እና በኮትዲቫር ኤስኢሲ ሚሞሳስ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያው ፋሲል ከነማ ሆኗል።
በ2025 ስምንት ጎሎች እና ሰባት ወደ ጎልነት የተቀየሩ ኳሶችን ማቀበል ችሏል፤ ለሶስት ተከታታይ አመታት በቤኒን ሻምፒዮን ሆኗል፤በ2022 የአመቱ ምርጥ ተጫዋችም በመሆን ተመርጧል።
አስተያየት ይስጡ