አዳማ ከተማ ዮሴፍ ታረቀኝን የግሉ አድርጓል።
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር ወደ ዝግጅት የገባው እና አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የቆየው አዳማ ከተማ ዮሴፍ ታረቀኝን የግሉ አድርጓል።

አዳማ ከተማ ከለቀቀ በኋላ በሁለት አመት ውስጥ ለሀዋሳ ከተማ ፣ መቻል እና ያለፉትን ስድስት ወራት ደግሞ በሸገር ከተማ መቆየት የቻለው የመስመር አጥቂው በመጨረሻም ወደ ቀደመ ክለቡ በሁለት አመት ውል ተመልሷል።
አስተያየት ይስጡ