ሸገር ከተማ ልምምድ የሚጀምሩበት ቀን ታወቀ
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሁለተኛ አመት ተሳትፎን የሚያደርገው ሸገር ከተማ ነገ በይፋ ልምምዱን ይጀምራል።

በክረምቱ የአሰልጣኝ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን በዋና አሰልጣኝነት ውል በማራዘም የጀመረው እና በቀጣይም ወደ ዝውውሩ በመግባት ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገር የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር የፈፀመው ክለቡ በዛሬው ዕለት የቡድኑ አባላት በአዳማ ከተማ የተሰባሰቡ ሲሆን በነገው ዕለት ዕሮብ ነሐሴ 20/2018 ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው ይጀምራሉ።
አስተያየት ይስጡ