የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የኪሩቤል ወንድሙን ቀጣይ ክለብ ወስኗል።

ከሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የግራ መስመር ተከላካዩ ኪሩቤል ወንድሙ ጉዳይ ይጠቀሳል። በወልዋሎ የነበረውን ውል በማጠናቀቁ ለሀላባ ከተማ ለመጫወት ከተስማማ በኋላ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መልሶ ደግሞ በወልዋሎ ውሉን እንዳራዘመ የተነገረለት ተጫዋቹ ለሦስት ክለቦች መፈረሙን ተከትሎ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።
አሁን ባገኘነው መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ተጫዋቹ ለሀላባ ከተማ እንዲጫወት ማዘዙን ተከትሎ የህክምና ምርመራውን በሀላባ አጠናቆ ክለቡ ሰሞኑን በሚጀምረው ዝግጅት ተካፋይ እንደሚሆን ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ