ሀላባ ከተማ ሽመክት ጉግሳን እና ናትናኤል ሠለሞንን ወደ ስብስቡ አካቷል።
ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካሳደገው አሰልጣኙ በሽር አብደላ እንደማይቀጥል የታወቀው እና ካሊድ መሐመድን ዋና አሰልጣኙ ያደረገው ሀላባ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ሽመክት ጉግሳ ከረጅም አመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል። ሀላባ ከተማን በሚሊኒየሙ መግቢያ ማገልገል የቻለው የቀድሞው የአየር ሐይል ፣ ደደቢት ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በምድረገነት ሽረ ቆይታን ያደረገው የመስመር አጥቂው ከአመታት በኋላ ወደ ቀደመ ክለቡ ተመልሷል።
ሌላኛው የበርበሬዎቹ አዲሱ ፈራማ አጥቂው ናትናኤል ሠለሞን ሆኗል። የቀድሞው የንብ እና የተጠናቀቀውን አመት የሊጉ ክስተት በሆነው ነገሌ አርሲ ያሳለፈው ተጫዋቹ ቀጣይ መዳረሻውን ሀላባ ከተማ አድርጓል።
አስተያየት ይስጡ