ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝግጅቱን መቼ እንደሚጀምር ክለቡ አሳውቋል።
በቅርቡ ሰርቪያዊውን አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾን በይፋ በአምስት አመት ውል ያስፈረመው ቅዱስ ጊዮርጊስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረም የቻለ ሲሆን ቡድኑን ካጠናከረ በኋላ ለ2019 የውድድር ዘመን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቼ እንደሚጀምር ክለቡ አሳውቋል።

በዚህ መሠረት የክለቡ ተጫዋቾች በዛሬው ዕለት ከተሰባሰቡ በኋላ በነገው ዕለት ነሐሴ 13/2018 ቢሾፍቱ በሚገኘው ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ማለዳ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ