የህክምና ምርመራ ያደረገው አቡበከር ናስር ውጤቱ ከታወቀ በኋላ መቻልን ይቀላቀላል ።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ካየናቸው አስደናቂ አጥቂዎች መካከል አንዱ መሆን የቻለው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው አጥቂው አቡበከር ናስር ቀጣዩ መዳረሻው መቻል ለመሆን መቃረቡን ያገኘነውት መረጃ ይጠቁማል።

ከሐረር ሲቲ መነሻውን በማድረግ በኢትዮጵያ ቡና እጅግ አመርቂ አመታትን አሳልፎ በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ መጫወት የቻለው አጥቂው ከገጠመው አስከፊ ጉዳት በኋላ በመቻል አመራሮች ከፍተኛ ፍላጎት በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራን ማድረግ የቻለ ሲሆን ውጤቱ አመርቂ መሆን ከቻለ ቀጣዩ የመቻል ተጫዋች መሆኑን እንደሚረጋገጥ ያገኘውት ተጨማሪ መረጃ ያስረዳል።
አስተያየት ይስጡ