ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከተሳካላቸው ተጫዋቾች መካከል ኤርትራዊው ፈጣኑ አጥቂ አሊ ሱለይማን ይጠቀሳል።

ሀገሩን ወክሎ ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ዋንጫ ለባህርዳር ከተማ በመፈረም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር መተዋወቅ የቻለው እና በሀዋሳ ከተማ የተሳኩ ሦስት አመታትን በማሳለፍ በ19 ጎሎች የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ጎል አስቆጣሪ በመባል የተሸለመው ይህ አጥቂ በተጠናቀቀው አመት ወደ ግብፅ ሊግ ተካፋዩ እስማኤሊያ በማምራት እጅግ ድንቅ ጊዜን በግሉ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን 11 ጎሎችን በማስቆጠርም የግብፅ ሊግ ሁለተኛ ጎል አግቢ ሆኖ መፈፀም በመቻሉ በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም የግብፅን ሊግ 5ኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለውን አል መስሪን በይፋ መቀላቀሉን ተጫዋቹ በስልክ ያደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ