አሚር ሙደሲር ውሉን ለተጨማሪ አመት አራዘመ።
ከዛሬ ጀምሮ በዝውውሩ ላይ የነቃ ተሳትፎን የሚያደርጉት ፋሲል ከነማዎች የአሚር ሙደሲርን ውል ለተጨማሪ ሁለት አመት አራዝመዋል።

ከኢትዮጵያ መድን ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በኢኮስኮ እና ገላን እንዲሁም በድጋሚ ተመልሶ መድንን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ካደረጉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን የቻለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በፋሲል ከነማ የሁለት አመት ቆይታው በመጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ለሁለት ተጨማሪ አመት ውሉን አድሷል።
አስተያየት ይስጡ