ሀላባ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች በማስፈረም ዝውውሩን ገፍቶበታል።
በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ ከገቡ በኋላ ካሌብ አማንኩዋ ፣ ኮንኮኒ ሀፊዝ እና ኪሩቤል ወንድሙን የግሉ ያደረገው ሀላባ ከተማ አራተኛው ፈራሚ ነስረዲን ሐይሉ ሆኗል።
የቀድሞው የገላን ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል የመሐል ተከላካይ በተጠናቀቀው አመት አጋማሽ ከመቻል ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን ቀጣዩ ማረፊያው ደግሞ አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ